መሶብ የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት ተመርቋል

የደሴ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።

የደሴ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርዕስ መስተዳድር ክቡር አረጋ ከበደ ሌሎች የፌዴራል፣ የክልልና የደሴ ከተማ የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተመርቋል።

የደሴ አንድ መሶብ አገልግሎት ሕዝብ ሩቅ ሳይሄድ ከመንግሥት ማግኘት የሚጠበቅበትን አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኝ ለማስቻል ያለመ አገልግሎቱ በተቋማት የሚስተዋለውን ብልሹ የአገልግሎት አሰጣጥ የሚያሻሽል ነው።

የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ 16 ተቋማትን በውስጡ የያዘ 70 በላይ አገልግሎቶችንም የሚሰጥ እንደሆነ ታውቋል።

አገልግሎቱ በሲስተም የተያያዘ ስለኾነ ተግባራትን በፍጥነት እና በጥራት ይሰጣል። ደንበኞች በፍጥነት ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ መጡበት መመለስ የሚችሉበት ፈጣን እና ቀልጣፋ አሠራርን የያዘም ነው።

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት እና የሕዝብን መስተጋብር እንደሚያሻሽል ታስቦ ተቋቁሞ እየተሠራበት ይገኛል፤ አገልግሎቱ ወጭን እና ጊዜን ቆጣቢ፣ ቀልጣፋ እና እርካታን የሚያረጋግጥ አሠራር ነው።

Share this Post